explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጉዳትን በማንኛውም አይነት መገለጫው ይሁን ከነፍስ ላይም ይሁን ከሌሎች ላይ መከላከል ግዴታ እንደሆነ ገለፁ። ስለሆነም አንድ ሰው ራሱንም ይሁን በተመሳሳይ መልኩ ሌላንም ቢሆን ማወክ አይፈቀድለትም። እንዲሁም ጉዳትን በጉዳት መመለስም አይፈቀድለትም። ምክንያቱም ወሰን ባልታለፈበት የማመሳሰል (የቂሷስ ህግ) ካልሆነ በስተቀር ጉዳት በመጉዳት አይወገድምና። ከዚያም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰዎችን ለሚጎዳ ሰው ጉዳት እንደሚያገኘው፤ ሰዎችን ለሚያጨናንቅም መጨናነቅ እንደሚያገኘው ዛቱ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ከማመሳሰል (ከደረሰበት በደል) በበዛ መልኩ መበቀል መከልከሉን እንረዳለን።
  • አላህ ባሮቹን በአንዳችም የሚጎዳቸው በሆነ ነገር አላዘዛቸውም።
  • በንግግር ወይም በተግባር ወይም በመተውም ቢሆን አውቆም ይሁን ሳያውቁ መጉዳት ተከልክሏል።
  • ምንዳ በስራው አይነት ነው የሚሰጠው። የጎዳ ሰው አላህ ይጎዳዋል ፤ ያስጨነቀም አላህ ያጨናንቀዋል።
  • ከሸሪዐ መርሆዎች መካከል አንዱ: - "ጉዳት መወገድ ይገባዋል።" የሚል ነው። ሸሪዓ በፍፁም ጉዳትን እንደማያፀናና መጉዳትን እንደሚያወግዝ እንረዳለን።