explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በነዚህ ትላልቅ ቃላቶች አላህን ማወደስ ከዱንያና በውስጧ ካለው ሁሉ የተሻለ መሆኑን ተናገሩ። እነሱም: "ሱብሓነሏህ" ይህም አላህን ከጉድለት ማጥራት ነው። "አልሐምዱሊላህ" ይህም አላህን ከመውደድና ከማላቅ ጋር በምሉዕ ባህሪያቶቹ ማወደስ ነው። "ላኢላሃ ኢለሏህ" ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። "አሏሁ አክበር" አላህ ከሁሉም ነገር የበለጠ ታላቅ ነው ማለት ነው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • አላህን በማውሳት ላይ መነሳሳቱ። አላህን ማውሳት ፀሀይ የወጣችበት ክልል ሁሉ ከሚሰጠን የበለጠ ተወዳጅ ነውና።
  • ውዳሴ ማብዛት ደረጃና ምንዳ ስላለው በርሱ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  • የዱንያ መጣቀሚያ ትንሽ ነው። ስሜትን የሚያስደስቱ ነገሮቿ ጠፊ ናቸው።