ጃቢር ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ማለቱ ተላልፏል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፡ "በላጩ ዚክር 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ማለት ሲሆን በላጩ ዱዓእ ደግሞ 'አልሐምዱሊላህ' ማለት ነው።'" ሐሰን ነው። - ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በኩብራ ውስጥ፣ ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።