ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወደ ጁመዓ ሶላት ማልዶ የመሄድን ትሩፋት ተናገሩ። መማለዱም ፀሐይ ከወጣችበት ወቅት ጀምሮ ኢማሙ ለኹጥባ እስከሚመጣበት ወቅት ይቆያል። ይህም አምስት ወቅቶች ይኖሩታል። አከፋፈሉም ፀሐይ ከወጣችበት ወቅት ኢማሙ መስጂድ ገብቶ ለኹጥባ ሚንበር ላይ እስኪወጣ ያሉትን ወቅቶች ለአምስት በመክፈል ይገኛል። የመጀመሪያው: እንደ ጀናባ ትጥበት የተሟላ ትጥበትን ከታጠበ በኃላ በመጀመሪያው ወቅት ጁሙዓ ወደሚሰግድበት መስጂድ የሄደ ሰው ሲሆን ይህም ግመል ሶደቃ እንደሰጠ ሰው ነው። ሁለተኛው: በሁለተኛው ሰዓት የሄደ ሲሆን ይህም ከብት እንደመፀወተ ሰው ነው። ሶስተኛ: በሶስተኛው ሰዓት የሄደ ሰው ሲሆን ይህም ቀንዳም ሙክት እንደመፀወተ ሰው ነው። አራተኛ: በአራተኛው ሰዓት የሄደ ሰው ሲሆን ይህም ዶሮ እንደመፀወተ ሰው ነው። አምስተኛ: በአምስተኛው ሰዓት የሄደ ሰው ሲሆን ይህም እንቁላል እንደመፀወተ ሰው ነው። ኢማሙ ለኹጥባ የወጣ ጊዜም መስጂድ በር ላይ ተቀምጠው መስጂድ ለሚገቡ ሰዎች አንድ በአንድ የሚጽፉ መላዕክቶች መመዝገባቸውን ትተው ዚክርና ኹጥባ ለማዳመጥም ይመጣሉ።