ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "የጁሙዐ ቀን ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ሳለ ለባልደረባህ 'ዝም በል!' ካልከው በርግጥም ውድቅ ንግግርን ተናግረሀል።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።