ዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሸመደዱትን አስር የሱና ረከዓዎች ገለጹ። እነዚህ ሱናዎች "ሱነን አርረዋቲብ" (ከግዴታ ሶላት በፊት ወይም በኋላ የሚሰገዱ ሱና ሶላቶች) ተብለው ይጠራሉ። ሁለት ረከዓ ከዙህር በፊትና ሁለት ረከዓ ከዙህር በኋላ፤ ከመግሪብ በኋላ ሁለት ረከዓ ቤታቸው ውስጥ፤ ሁለት ረከዓ ከዒሻ ሶላት በኋላ ቤታቸው ውስጥ፤ ከፈጅር በፊት ሁለት ረከዓ ይሰግዱ ነበር። ይህም አስር ረከዓ ሞላ። ከጁመዓ ሶላት በኋላም ሁለት ረከዓ ይሰግዱ ነበር።