ከዐብደላህ ቢን ማሊክ ኢብኑ ቡሐይና (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሚሰግዱ ጊዜ የብብታቸው ንጣት ግልፅ እስኪሆን ድረስ በእጆቻቸው መካከል ይከፍቱ ነበር። ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።