explain-icon

ትንታኔ

በማንኛውም ወቅትና ለማንኛውም አላማ መስጂድ የመጣና የገባ ሰው ከመቀመጡ በፊት ሁለት ረከዓ እንዲሰግድ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አነሳሱ። ይኸውም ሁለቱ የተሒየተል መስጂድ ረከዓዎች ናቸው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ከመቀመጥ በፊት የተሒየተል መስጂድ ሁለት ረከዓ መስገድ እንደሚወደድ እንረዳለን።
  • ይህ ትእዛዝ መቀመጥ ለፈለገ ሰው ነው። መስጂድ ገብቶ ሳይቀመጥ የወጣን ሰው ትእዛዙ አይመለከተውም።
  • አንድ ሰጋጅ ሰዎች ሶላት ውስጥ ሆነው መስጂድ ቢገባና ቀጥታ እነርሱ ወደሚሰግዱት ሶላት ቢገባ ከሁለቱ የተሒየተል መስጂድ ረከዓ ያብቃቃዋል።