ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ «እኛ ከአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ተቀምጠን ሳለ ድንገት አንድ የገጠር ሰው መጣና መስጂድ ውስጥ መሽናት ጀመረ። የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ባልደረቦችም "አተ! አተ!" አሉት። የአላህ መልክተኛም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - "አታቋርጡት ተዉት!" አሉ። ሸንቶ እስኪያጠናቅቅም ተዉት። ቀጥሎ የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጠሩትና እንዲህ አሉት: "እነዚህ መስጂዶች ለዚህ ሽንትና ቆሻሻ አይበጁም። እነዚህ የሚበጁት አላህን ለማውሳት፣ ለሶላትና ቁርአንን ለመቅራት ነው።" አሉት። ወይም የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ይህን የመሰለ ንግግር ተናገሩት። አንድን ሰው ውሃ የሞላ ባልዲ ይዞ እንዲመጣ አዘዙና እላዩ ላይ ደፉበት።» ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - መስጂዳቸው ውስጥ ከባልደረቦቻቸው ጋር ነበሩ። አንድ ባላገር ከገጠር መጣና የመስጂዱ ጎን ዘንድ ተቀምጦ መሽናት ጀመረ። ሶሓቦችም "አተ አቁም! ተው!" በማለት አስጠነቀቁት። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - "ተዉት! ሽንቱን አታቋርጡት።" አሉ። እስኪያጠናቅቅም ድረስ ተዉት። ከዚያም ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጠርተው እንዲህ አሉት: መስጂዶች ለሽንትና ለቆሻሻ አይነቶች አይበጁም። መስጂድ የሚበጀው አላህን ለማውሳት፣ ለሶላት፣ ቁርአንን ለመቅራትና ለመሳሰሉት ነው። ቀጥለው ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - አንድን ሶሓባ በውሃ የተሞላ ባልዲ ይዞ እንዲመጣ አዘዙና በቀላሉ ሽንቱ ላይ ደፉበት።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • መስጂዶችን ማላቅና ለመስጂድ የማይመጥኑ ከሆኑ ነገሮች መጠበቅ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
  • ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ከዚህ ሐዲሥ መስጂዶችን መጠበቅ፣ ከቆሻሻና አክታ ማፅዳት፣ ከጭቅጭቅ፣ ድምፅን ከፍ ከማድረግ፣ ከመሸጥ፣ ከመግዛት፣ ሌሎችንም ውሎች ከመዋዋልና ተመሳሳይ የሆኑ ነገሮችን ከመፈፀም መራቅ እንደሚገባ እንረዳለን።"
  • ለአላዋቂ ማዘንና ስህተቱ በንቀትና በትዕቢት የመጣ ካልሆነ በቀር የፈፀመውን ሳያጥላሉና ሳያውኩ ማስተማር እንደሚገባ እንረዳለን።
  • ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - አዛኝ አስተማሪ፣ ሩሕሩሕ አደብ የሚያሲዙ፣ ቻይ ሆነው የሚያንፁ ነበሩ።
  • የአላህን ቤቶች በሶላት፣ ቁርአንን በመቅራትና አላህን በማውሳት ማሳመር ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።