ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘይነብ ቢንት ጀሕሽ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- ዘንድ ደንግጠውና ፈርተው አስከፊ ክስተት እንደሚከሰት ለማሳወቅ ላኢላሃ ኢለሏህ እያሉ ገቡ። ከዚህ አስከፊ ክስተት ወደ አላህ በመጠጋት ካልሆነ በቀር መዳን አይገኝምና። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: መከሰቱ በቀረበው አደጋ ለዐረቦች ወዮላቸው፤ ዛሬ ዙልቀርነይን ገንብቶ ከዘጋው የየእጁጅና መእጁጅ ግድብ ይህን ያህል ተከፍቷል። በአውራ ጣታቸውና በሚቀጥለው ጣታቸውም ክብ አድርገው አሳዩዋት። ዘይነብም (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- "በመካከላችን ደጋጎችና አማኞች እያሉ እንዴት አላህ በኛ ላይ ጥፋትን ይሾምብናል?" አለች። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለርሷ "እንደ ዝሙት፣ አስካሪ መጠጥና ሌሎች የአመፅና የወንጀል ፀያፍ ተግባራት የበዙ ጊዜ ጥፋት ሁሉንም ያዳርሳል።" አሏት።