የአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ስለነበራት አንዳንድ ግላዊ ሁኔታዋ ተናገረች። ከዚህም ውስጥ: የጀናባ ትጥበትን ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ሁለቱም ከአንድ እቃ እየጨለፉ ይታጠቡ ነበር። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የወር አበባ ላይ ሆና ሳለ ለጨዋታ መቅረብ የፈለጉ ጊዜ ከእንብርት እስከ ጉልበቷ ያለውን ሰውነት እንድትሸፍን ያዟትና ከግንኙነት ውጪ ያለን ጨዋታ ይጫወቱ ነበር። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መስጂድ ውስጥ ኢዕቲካፍ ይገቡ ነበር። እናታችን ዓኢሻ በቤቷ ውስጥ የወር አበባ ላይ ሆና ሳለ ጭንቅላታቸውን ያወጡላትና ታጥባቸው ነበር።