የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህ ሃይማኖት የምድርን አጠቃላይ ክፍል እንደሚያዳርስ፣ ማንኛውም ሌሊትና ቀን የተፈራረቀበት ስፍራ ሁሉ ይህ እምነት እንደሚደርሰው ተናገሩ። አላህ አንድንም ከተማና መንደር ሆነ አልያም ገጠርና በረሃ ይህ እምነት እንዲገባበት ሳያደርግ እንደማይተወው ተናገሩ። ይህንን ሃይማኖት ተቀብሎ ያመነበት ሰው በእስልምና ልቅና የበላይ ይሆናል። ይህንን ሃይማኖት አልቀበል ያለና የካደበት ደግሞ የተዋረደና የበታች ይሆናል። ቀጥሎ ሶሐባው ተሚም አድዳሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ይህን የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የተናገሩበትን ጉዳይ ልዩ በሆነ መልኩ በቤተሰቦቹ ውስጥ እንዳስተዋለው ተናገረ። ከነርሱ መካከል የሰለሙት መልካምን፣ ክብርና ልቅናን ያገኙ ሲሆን ከነርሱ መካከል የካዱት ደግሞ ለሙስሊሞች ከሚሰጡት ገንዘብ ተጨማሪ ውርደትና የበታቸኝነትን አግኝቷቸዋል።