አቡ ሙሳ አልአሽዐሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከተወሰኑ የጎሳዎቹ ሰዎች ጋር በመሆን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ እንደመጡ ተናገሩ። የመምጣታቸው አላማም በጂሀድ ለመካፈል እንዲመቻቸው የሚጋልቡትን ግመል ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲሰጧቸው ለመጠየቅ ነው። እርሳቸውም መጓጓዣ እንደማይሰጧቸውና የሚሰጧቸው መጓጓዣም እንደሌላቸው ምለው ነገሯቸው። ተመለሱና የተወሰነ ጊዜ እንደቆዩ ለነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶስት ግመል መጣላቸው። ግመሎቹም ወደነርሱ ተላኩ። ከፊሎቹ ለከፊሉ: "አላህ በነዚህ ግመሎች ለኛ አይባርክልንና ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መጓጓዣ እንደማይሰጡን ምለው ሳለ እኛ እንዴት እንቀበላለን?" በመባባል መጥተው እርሳቸውን ጠየቁ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ: ለናንተ መጓጓዣውን የሰጣችሁ አላህ ነው። እርሱ ነው የገጠማችሁና የለገሳችሁ። እኔማ በእጃችሁ እንዲደርስ አማካኝ የሆንኩ ሰበብ ብቻ ነኝ። ቀጥለውም ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ: እኔ ወላሂ አላህ ከሻ በአንዳች የምሰራው ወይም በምተወው ነገር ላይ ምዬ ከዚያም ከዛ ከተማለለት ነገር ተቃራኒው የተሻለና በላጭ መሆኑን ካየው የተሻለውን ነገር ፈፅሜ የማልኩበትን ነገር እተወዋለሁ። ለመሀላዬም ማካካሻ አወጣለሁ።