ከእናትችን ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች፦ "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ "ምግብ ቀርቦ አልያም ሁለቱ ቆሻሻዎች እያጨናነቁት ሶላት የለም።" ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሰጋጅ ነፍስ የሚጓጓውና ልቡ የተንጠለጠለበት ምግብ ቀርቦ መስገድን ከለከሉ። ልክ እንደዚሁ በቆሻሻው ግፊት ስለሚጠመድም ሁለቱ ቆሻሾች እያጨናነቁት ከመስገድ ከለከሉ። (እነርሱም ሽንትና አይነ ምድር ናቸው።)

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • አንድ ሰጋጅ ወደ ሶላት ከመግባቱ በፊት ከሶላቱ የሚያዘናጋውን ነገር ባጠቃላይ ማራቅ ይገባዋል።