ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሶላት ውስጥ ሆነው ዱዓ ሲያደርጉም ይሁን ሌላ ድርጊት ሲያደርጉ አይኖቻቸውን ወደ ሰማይ ከፍ የሚያደርጉ ሰዎችን አስጠነቀቁ። ቀጥለውም ይህንን በሚፈፅሙ ሰዎች ላይ ማስጠንቀቂያቸውንና ዛቻቸውን አበረቱ። በማያውቁት መልኩ የማየትን ፀጋ በሚያጡበት ሁኔታ አይኖቻቸውን የመነጠቅና በፍጥነት የመጥፋት አደጋ እንደሚፈራለትም አሳሰቡ።