አቡ ሙሳ አልአሽዓሪይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተናገሩት: ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ወደ የመን ላኩት። በየመን መሬት ስለሚሰራ መጠጥ ክልክል ስለመሆኑ ጠየቃቸው። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ስለመጠጡ ምንነት ዝርዝር ጉዳይ ጠየቁት። አቡ ሙሳም - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - "ቢትዕ ከማር የሚሰራ አስካሪ መጠጥ ሲሆን ሚዝር ደሞ ከገብስ የሚሰራ አስካሪ መጠጥ ነው።" ብለው ተናገሩ። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ንግግርን ሰብስቦ የመናገር ተሰጥዖ ተሰጥቷቸዋልና "ሁሉም አስካሪ ሐራም ነው።" አሉት።