ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ማንኛውም አይምሮን የሚያደነዝዝና የሚያስወግድ የሚጠጣም ይሁን የሚበላም ይሁን የሚሸተት ወይም ከዚህ ውጪ ያለ ነገር ሁሉ ኸምርና አስካሪ መሆኑን ገለፁ። ሁሉም አስካሪና አይምሮን የሚያስወግድ ነገርም አነሰም በዛም አላህ ከልክሎታል። ከነዚህ የአስካሪ አይነቶች መካከል ማንኛውንም አይነት የወሰደና በመውሰድ ላይም የዘወተረ እስኪሞት ድረስም ንስሀ ያልገባ ሰውም ጀነት ውስጥ መጠጣትን በመነፈግ የአላህ ቅጣት ይገባዋል።