ከጃቢር ቢን ዐብደሏህ ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፡ «የአሏህ መልዕክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል፡ "ሲበዛ ያሰከረ ነገር ትንሹ ክልክል ነው።" ሐሰን ነው። - አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አብዝቶ ሲወሰድ አይምሮን የሚያስወግድ ማንኛውም የሚጠጣ ወይም የሚበላ ነገር ሁሉ አይምሮን የሚያስወግድበትን ያህል መጠን የማይደርስ ትንሽ እንኳ መውሰድ ክልክል መሆኑን ገለፁ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ሸሪዓ የሰዎችን አይምሮ እንደጠበቀ እንረዳለን።
  • ወደ ክልክል የሚያደርሱ መንገዶችን መዝጋት የሚለው መርህ በትክክል የሚተገበር መሆኑን እንረዳለን። ይህም ሁሉንም ወደዚህ ቆሻሻ ነገር የሚያደርሱን መንገዶች ሁሉ በመዝጋት ነው።
  • አስካሪን ነገር በጥቂቱ እንኳ መውሰድ ወደ ስካር መንገድ የሚያደርስ ስለሆነ መከልከሉን እንረዳለን።
  • በትንሹም ሆነ አብዝቶ ቢወሰድ የማያሰክር ነገር ክልክል አለመሆኑን እንረዳለን።