ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የትንሳኤ ቀን ፀሐይ ወደ ፍጡራን ከጭንቅላታቸው በላይ የማይል ያህል እንደምትቀርብ ተናገሩ። ታቢዒዩ ሱለይም ቢን ዓሚርም እንዲህ አለ: በአላህ እምላለሁ! የአላህ መልክተኛ ሚል የሚለው ቃል ከሚሰጠው ሁለት ትርጓሜዎች የትኛውን እንደፈለጉበት አላውቅም። የምድር ርቀት መለኪያውን ማይል ነው ወይስ አይን መኳያውን ሚል ነው የፈለጉበት የሚለውን አላውቅም። እንዲህም አሉ: "በስራቸው ልክም በላብ ውስጥ ይጠመቃሉ። ከነርሱ መካከል ላቡ እስከቁርጭምጭሚቱ ድረስ የሚሆን አለ፤ ከነርሱም መካከል ላቡ እስከጉልበቱ ድረስ የሚሆን አለ፤ ከነርሱም መካከል ላቡ እስከሽርጥ መታጠቂያው እስከ ወገቡ ድረስ የሚሆን አለ፤ ከነርሱም መካከል ላቡ እስከ አፉ ድረስ የሚሆንና መናገር የሚከለክለው አለ።" ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህንን ብለው በእጃቸው ወደ አፋቸው ጠቆሙ።