explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሙስሊሞች ከአይሁዶች ጋር ሳይዋጉ በፊት ሰዓቲቱ እንደማትቆም ተናገሩ። አይሁዱ ከሙስሊሞች ለመሸሸግ ብሎ ወደ አንድ ድንጋይ የሸሸም ጊዜ ድንጋዩ ሙስሊሙን እንዲጣራና ከኋላው አይሁድ ስላለ መጥቶ እንዲገድለው የመናገር አቅም አላህ ለድንጋዩ ይሰጠዋል።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አላህ ባሳወቃቸው መጠን አንዳንድ የሩቅና የወደፊት ጉዳዮች መናገራቸውን። ይህም መከሰቱ የማይቀር ጉዳይ መሆኑን፤
  • በመጨረሻ ዘመን ሙስሊሞች ከአይሁዶች ጋር እንደሚዋጉና ይህም የቂያማ ምልክት መሆኑን፤
  • የእስልምና ሃይማኖት እስከ ዕለተ ቂያማ እንደሚቆይና ከሁሉም ሃይማኖት የበላይ እንደሚሆን ፤
  • አላህ ሙስሊሞችን በጠላቶቻቸው ላይ እንደሚረዳቸው፤ ከዚህም ውስጥ በመጨረሻው ዘመን ድንጋዩ እንዲናገር በማድረግ መርዳቱ ይጠቀሳል።