ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አንድ ሰው በአንድ ሰው ቀብር በኩል እያለፈ 'ዋ ምኞቴ ምናለ በርሱ ስፍራ ላይ እኔ በነበርኩ!' እስኪል ድረስ ሰአቲቱ አትቆምም።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ሰውዬው በቀብር በኩል እያለፈ ሞቶ በተቀበረው ፋንታ ሞቶ በነበር እስኪመኝ ድረስ ሰአቲቱ እንደማትቆም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ተናገሩ። የዚህ ምክንያትም ጥመትና የጥመት ባለቤቶች በመብዛታቸው፣ ፈተና፣ ወንጀልና ውግዝ ተግባራት ይፋ በመሆናቸው ሳቢያ ኢማኑ እንዳይጠፋ በነፍሱ ላይ በመፍራቱ ነው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • በመጨረሻው ዘመን ወንጀሎችና ፈተናዎች ይፋ እንደሚሆኑ መጠቆሙን እንረዳለን።
  • ጥንቃቄ በማድረግ፣ በኢማንና በመልካም ስራ ለሞት መዘጋጀት እና ከፈተናና መከራ ስፍራዎች መራቅ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።