ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የሙናፊቅን ሁኔታ ከሁለት የፍየል መንጋ የትኛውን የፍየል መንጋ መከተል እንዳለባት እንዳላወቀች አንድ ፍየል አምሳያ እንደሆነ ገለፁ። ወደዛ መንጋ አንዴ ትሄዳለች ወደሌላኛው ደግሞ ሌላ ጊዜ ትሄዳለች። እነሱም በኢማንና ክህደት መካከል የዋለሉ ናቸው። በውጫዊና ውስጣዊ ማንነታቸው ከአማኞችም ጋር አይደሉም ከከሀዲዎችም ጋር አይደሉም። በተቃራኒ ውጫቸው ከአማኞች ጋር ሲሆን ውስጣቸው በጥርጣሬና ማወላወል የተሞላ ነው። ልባቸው አንዳንዴ ወደ አማኞች ሲዘነበል አንዳንዴ ደግሞ ወደከሀዲያን ይዘነበላል።