ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከርሳቸው የተማርነውን ቁርአናዊም ይሁን ሐዲሣዊ እውቀት አንድ አንቀፅ ያህል ትንሽ እንኳ ቢሆን እንድናስተላልፈው አዘዙን፤ ይህም ግን የምንጣራበትንና የምናደርሰውን መልእክት ተረድተነው መሆኑ ቅድመ መስፈርቱ ነው። ከዚያም ሽሪዓችን ጋር እስካልተጋጨ ድረስ ከበኒ ኢስራኢሎች የተከሰተባቸውን ክስተትና መሰል ጉዳዮችን በተመለከተ ማውራታችንም ችግር እንደሌለው ገለፁ። ከዚያም በሳቸው ላይ ከመቅጠፍ አስጠነቀቁ፤ ሆን ብሎ በሳቸው ላይ የዋሸም ጀሀነም ውስጥ ማረፊያውን እንዲይዝ አሳሰቡ።