ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሰዎች እንዲሰሙዋቸውና እንዲታዘዟቸው ሐቃቸውን ከሰዎች እየፈለጉ፤ በነርሱ ላይ ያለባቸውን ፍትህ ማስፈንን፣ ምርኮን ማከፋፈልን፣ ግፍን በመከላከል እኩልነት የመፍጠርን ሐቅ ግን ስለሚከለክሉ መሪዎች ከነርሱ ጋር ምን እንድናደርግ እንደሚያዙን ተጠየቁ። ነቢዩም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህንን ጥያቄ እንደጠሉ በሚያሳብቅ መልኩ ከርሱ ዘወር አሉ። ጠያቂው ግን ለሁለተኛና ለሶስተኛ ጊዜ ጥያቄውን ደገመላቸው። አሽዐሥ ቢን ቀይስም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና - ጠያቂውን ዝም ለማስባል ጎተተው። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሲመልሱለት እንዲህ አሉ: "የመሪዎቻችሁን ንግግር ስሙ፤ ትእዛዛቸውን ታዘዙ። በነርሱም ላይ የተጣለባቸው ፍትህን የማስፈን፣ የህዝብን ሐቅ የማሟላት ኃላፊነት አለባቸው። በናንተም ላይ የተጣለባችሁ የመታዘዝ፣ ሐቃቸውን የመወጣት፣ በሚያደርሱት ግፍ ላይ የመታገስ ግዴታ አለባችሁ።