ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሁሉ ቀን ጎህ ከቀደደ በኋላ ንጋት ላይና ፀሀይ ከመግባቷ በፊት ደግሞ ሁሌ ምሽት ላይ ሶስት ጊዜ ይህንን ዚክር ያለ ሰው:(ቢስሚላሂ) በአላህ ስም ከሁሉም ጎጂ ነገር እጠበቃለሁም እታገዛለሁም። (ያ ስሙን ከማውሳት ጋር) ምንም ያህል ቢተልቅ (አንዳችም የማይጎዳው) (በምድርም ውስጥ) ከምድር የሚወጡ በሆኑ መከራዎችም (በሰማይ ውስጥም) ከሰማይ የሚወርዱ በሆኑ መከራዎችም (እርሱ ንግግራችንን ሰሚ) ሁኔታችንንም (አዋቂ ነው።) የምንጎዳ አይደለንም። በሚያመሽ ወቅት የተናገራት እስኪያነጋ ድረስ ድንገተኛ መከራ አያገኘውም። በሚያነጋ ወቅት የተናገራት ደግሞ እስኪያመሽ ድረስ ድንገተኛ መከራ አያገኘውም። ሐዲሡን ያወራው አባን ቢን ዑስማንን በወቅቱ የሰውነቱ ግማሽ ሽባ የመሆን በሽታ አጋጥሞት ስለነበር ከርሱ ይሄን ሐዲሥ የሰማው ሰውዬም በግርምት አይን ተመለከተው። አባንም ለሰውዬው እንዲህ አለው "እንደዚህ የምትመለከተኝ ምን ሆነህ ነው? በአላህ እምላለሁ! በዑሥማንም ላይ አልዋሸሁም። ዑሥማንም በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ አልዋሸም። ነገር ግን ይህ በሽታ ባጋጠመኝ እለት አላህ እንድለው አልወሰነልኝም ነበር። የሚያስቆጣ ነገር አጋጠመኝና እነዚህን የተጠቀሱ ቃላቶች ማለትን ዘነጋሁኝ።"