ታላቁ ሶሐባ ዐብደላህ ቢን ኹበይብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና በርካታ ዝናብ በሚዘንብበትና ድቅድቅ ጨለማ በነበረበት ምሽት የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲያሰግዷቸው ፈልገው እንደወጡና እንዳገኟቸው ተናገረ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለርሱ "በል!" ማለትም አንብብ! አሉት። እርሱም ምንም አላነበበም። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ንግግራቸውን ሲደጋግሙለት ዐብደላህም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምን ልቅራ?" አላቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ሱረቱል ኢኽላስን እና ሁለቱን መጠበቂያዎች ሱረቱል ፈለቅ እና ሱረቱ አን-ናስን በምሽት ወቅትና በንጋት ወቅት ሶስት ጊዜ ቅራ! ከሁሉም ክፋትና ጉዳት ይጠብቅሃል።" አሉት።