ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከነዚህ ሶስት አካላት በቀር የአደም ልጆች ሁሉ ተጠያቂነት እንደማይቀርላቸው ተናገሩ። ጨቅላ ህፃን ልጅ እስኪተልቅና አቅመ አዳም እስኪደርስ ድረስ፤ አይምሮውን ያጣ እብድ አይምሮው ወደርሱ እስኪመለስለት ድረስ፤ እንቅልፉን የተኛ ሰው እስኪነቃ ድረስ ናቸው። ከነዚህ አካላት ተጠያቂነት ተነስቷል። ወንጀል ቢሰሩ በነርሱ ላይ አይፃፍም። ነገር ግን ከእብድና ከተኛ ሰው ውጪ ትንሽ ህፃን ልጅ መልካም ስራ ከሰራ ይፃፍለታል። ይህም እብድና የተኛ ሰው አይምሮዋቸው ስለተወገደ አምልኮን አስተካክለው የሚፈፅሙ አካላት ስላልሆኑ ነው።