ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መስጂድ በሚገቡ ወቅት እንዲህ ይሉ ነበር: (አዑዙ ቢላሂል ዐዚም) በአላህና በባህሪያቱ እከለላለሁ፣ እጠበቃለሁም። (ወቢወጅሂሂል ከሪም) ሰጪና ቸር በሆነው፤ (ወሱልጧኒሂ) ከፍጡራኖች መካከል በፈለገው ላይ ባለው አሸናፊነቱ፣ በችሎታውና በበላይነቱ (አልቀዲም) የመጀመሪያና ዘላለማዊ በሆነው፤ (ሚነሽ-ሸይጧኒ ረጂም) ከአላህ እዝነት የተባረረና የራቀ ከሆነው ሰይጣን እጠበቃለሁ። ማለትም: አላህ ሆይ! ከሰይጣን ጉትጎታ፣ ከማጥመሙ፣ ከእርምጃዎቹ፣ ውስጣችን ላይ ከሚፈጥረው ውልታና ማጥመም ጠብቀኝ ማለት ነው። ይህም የጥመት ምክንያትና ለመሀይምነትና መጥመም የሚያነሳሳው (ጠንሳሽ) እርሱ ስለሆነ ነው። ለዐብደላህ ቢን ዐምርም "ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያሉት ይህን ብቻ ነውን?" ተብሎ ተጠየቀ። እርሱም "አዎን" አለ። መስጂድ የሚገባ ሰው ይህን ዱዓ ካለም ሰይጣን እንዲህ ይላል: ይህ መስጂድ የገባው ሰው ነፍሱን በአጠቃላይ ወቅቱ ቀኑንም ምሽቱንም ከኔ ጠብቋታል።