ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶሐቦች እንዲሰሩ፤ ወሰን ሳያልፉና ሳያጓድሉ በቻሉት ልክ አላህንም እንዲፈሩ፤ ስራቸው ተቀባይነት አግኝቶ በነርሱ ላይ የአላህ እዝነት እንዲወርድ ሰበብ እንዲሆንም በስራቸው ለአላህ በማጥራትና ሱናን በመከተል በትክክል መስራትን እንዲያስቡ አነሳሱ። ቀጥለውም ከናንተ መካከል አንድም ሰው በስራው ብቻ አይድንም። ይልቁንም የግድ የአላህ እዝነት ያስፈልገዋል ብለው ነገሯቸው። ሰሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የእርሶ ሥራ እንዲህ መጠኑ ከመግዘፉ ጋርም (መልካም ስራዎ ብቻውን) አያድኖትምን?" አሉ። እርሳቸውም "እኔም ብሆን አላህ በችሮታውና በእዝነቱ እስካልሸፈነኝ ድረስ በስራዬ ብቻ አልድንም።" አሉ።