ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአላህ ድንበር ላይ ለቆሙ፣ በአላህ ትእዛዝ ላይ ቀጥ ላሉ፣ በመልካም ለሚያዙና ከመጥፎ ለሚከለክሉ ሰዎች ምሳሌ አደረጉ። የአላህን ድንበር የሚተላለፉ፣ መልካምን የተዉና ውግዝን የሚተገብሩ ሰዎች በማህበረሰቡ መዳን ላይ የሚያሳድሩት አሻራ ምሳሌው በመርከብ እንደተሳፈሩ ሰዎች ምሳሌ ነው። የመርከቡ የላይኛው ክፍልና የታችኛው ክፍል የሚቀመጠውን ለመወሰን እጣ ተጣጣሉ። ከፊሉ የላይኛው ክፍል ሲደርሰው ከፊሉ ደግሞ ታችኛው ክፍል ደረሰው። ከታች በኩል ያሉት ውሃ ማምጣት የፈለጉ ጊዜ ከላያቸው ወዳሉት ያልፉ ነበር። ከታች በኩል ያሉት "ባለንበት ስፍራ ከታች ብንቀደው ኖሮ በርሱ በኩል ውሃ እናገኝ ነበር። ከላያችን ያሉትንም አናስቸግርም ነበር።" አሉ። ከላይ በኩል ያሉት ይህንን እንዲፈፅሙ ከተዉዋቸው ሁሉንም እንደያዘች መርከቧ ትሰምጣለች። ከዚህ ተግባራቸው ለመከልከል ቆመው ማቀብ ከቻሉ ደሞ ሁለቱም ክፍሎች ባጠቃላይ ይድናሉ።