ከምእመናን እናት ዓኢሻ -አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች፦ "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጠቅለል ያሉ ዱዓዎችን ማድረግ ይወዱ ነበር። ከዚህ ውጪ ያለውንም ይተዉ ነበር።" ሶሒሕ ነው። - አቡዳውድና አሕመድ ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የዱንያንም ሆነ የመጪውን አለም መልካም ነገር የጠቀለለ አላህ ላይ ማወደስና መልካም ፍላጎቶችንም ያካተተ ሁኖ ቃሉ አንሶ ሀሳቡ የበዛ ዱዓን ማድረግ ይወዱ ነበር። ከዚህ ውጪ ያለንም ይተዉ ነበር።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ዱዓን በጥቂትና በርካታ ሀሳቦችን በሰበሰቡ ቃላቶች ማድረግ እንደሚወደድ፤ ዱዓ ላይ የቃላት ስንጠቃና ከአቅም በላይ መጣጣርም እንደሚጠላ የነቢዩንም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) መመሪያ መቃረን ነው።
  • የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በጠቅላይ ቃላቶች ተለይተዋል።
  • ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዱዓ እንዳደረጉበት የተረጋገጡ ዱዓዎች ላይ ቢረዝምና ቃሉ ቢበዛ እንኳ ያንን ዱዓ ማድረግ ላይ ጥረት ማድረግ እንደሚገባ ተረድተናል።