ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዱዓእ ስናደርግ እጅን ከፍ በማድረግ ላይ አነሳሱ። አላህ (ሐይዩን) እጅግ በጣም የሚያፍር፤ መስጠትን የማይተው፤ ለባሪያው የሚያስደስተውን የሚያደርግና የሚጎዳውን የሚያስቀርለት ነው። (ከሪሙን) ሳይጠየቅ የሚሰጥ ቸር ነው። ከተጠየቀ በኋላስ (እንዴት ሊመልሰው ይሆን)?! አማኝ ባሪያው ለዱዓ ሁለት እጆቹን አንስቶ ለምኖት ለርሱ ባዶ አድርጎ መመለስን ያፍራል።