ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አንድ ሙስሊም ወንጀልና በደል ለመፈፀም እንዲገራለት መለመንን የመሰለ ወንጀል ባልሆነ፤ በቅርብ ዘመዱና በልጆቹ ላይ እርግማን መለመንን የመሰለ ዝምድና መቁረጥ ባልሆነ ዱዓእ አላህን የለመነና የጠየቀ ጊዜ አላህ በዱዓው አማካይነት ከሶስት ነገሮች አንዱን ይሰጠዋል ብለው ተናገሩ፡ ወይ የለመነውን በፍጥነት ይሰጠዋል፤ ወይም የትንሳኤ ቀን ደረጃውን ከፍ እንዲያደርግለት ወይም እንዲታዘንለትና ወንጀሉን መማሪያ እንዲሆንለት አላህ ምንዳውን ያደልብለታል፤ ወይም የለመነውን የሚያክል የሆነ መጥፎን ነገር በዱንያው ውስጥ ይከላከልለታል። ሶሐቦችም ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "ስለዚህ ከነዚህ ደረጃዎች አንዱን እንድናገኝ ዱዓን እናብዛ እንዴ?" አሉ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "አላህ ዘንድ ያለው እናንተ ከምትጠይቁትም በላይ ትልቅና ብዙ ነው። የርሱ ስጦታ አያልቅምም አይቀንስምም።" አሏቸው።