የተከበሩት ነቢይ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከህክምና መሰረቶች አንዱን መሰረት ጠቆሙን። ይህም የሰው ልጅ ጤናውን የሚጠብቅበት መጠበቂያ ነው። እሱም አመጋገብን ማሳነስ ነው። እንደውም አንጀቱን የሚዘጋለትን ያህልና የግዴታ ስራዎቹ ላይ የሚያበረታውን ያህል ይመገብ። ከሚሞሉ ቋቶች ሁሉ መጥፎው ሆድ ነው። ይህም በመጥገቡ ምክንያት በወቅቱ ወይም ዘግይቶ፣ ውጫዊም ይሁን ውስጣዊ ተቆጥረው የማያልቁ አደገኛ መዘዞችን ስለሚያመጣ ነው። ቀጥለውም መልክተኛው -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ አሉ: የሰው ልጅ የግድ መጥገብ አለብኝ ካለም የሚመገበውን ምግብ የሆዱ ሲሶውን ያህል ያድርግ። የተቀረውን ሲሶ ደግሞ ለመጠጡ ያድርገው። መጣበብና ጉዳት እንዳይደርስበት፣ አላህ ግዴታ ያደረገበትን የዲኑ ወይም የዱንያ ጉዳዩን ከመፈፀም እንዳያሳንፈው ሲል ሲሶውን ደግሞ ለትንፋሹ ያድርግለት።