አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለጂሀድና ለጦርነት ከአላህም ምንዳን ፈልጎ ሰዎች ዘንድም መሞገስና መወደስን ከጅሎ ስለሚወጣ ሰው ብይን ሊጠይቅ ፈታዋ ፈልጎ መጣ። ምንዳ ያገኛልን? ሲልም ጠየቃቸው። የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በኒያው ከአላህ ውጪ ስላጋራ ለርሱ አንዳችም ምንዳ እንደሌለው መለሱለት። ሰውዬውም ሶስት ጊዜ ጥያቄውን ደገመላቸው። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለርሱ ምንም ምንዳ እንደሌለው አፅንዖት በመስጠት ተመሳሳይ መልስ መለሱለት። ቀጥለውም ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የትኛውም ስራ አላህ ዘንድ ምንዳና ተቀባይነት የሚያገኝበትን መርህ ነገሩት። የትኛውም ስራ በአላህ ላይ አንድም ሳይጋራበት ሙሉ በሙሉ ለአላህ የሆነና ለርሱ ፊት ብቻ ተብሎ የተሰራ እስካልሆነ ድረስ አላህ ስራውን እንደማይቀበለው ነገሩት።