ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አንዳችሁ የበላ ጊዜ በቀኙ ይብላ። የጠጣም ጊዜ በቀኙ ይጠጣ። ሰይጣን የሚበላውም በግራው፤ የሚጠጣውም በግራው ነውና።" ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።