ሑዘይፋ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳወሱት: ከነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ማዕድ ለመጋራት በተገኙ ጊዜ የአላህ መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እጃቸውን ወደ ማዕዱ ከመስደዳቸውና ከመጀመራቸው በፊት እነርሱ እጃጀውን አይሰዱም ነበር። አንድ ቀን ከርሳቸው ጋር ማዕድ ለመጋራት ተገኘን። ከፍጥነቷ የተነሳ አመጣጧ ልክ እየተገፈተረች በሚመስል መልኩ የሆነች አንዲት ሴትዮ መጣችና እጇን ወደ ማዕዱ ሰደደች። የአላህ መልክተኛም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እጇን ያዟት። ቀጥሎም ከፍጥነቱ የተነሳ አመጣጡ ልክ እየተገፈተረ በሚመስል መልኩ የሆነ አንድ የገጠር ሰውዬ መጣና እጁን ወደ ማዕዱ ሰደደ። የአላህ መልክተኛም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ምግቡን ከመንካቱ በፊት እጁን ያዙትና እንዲህ አሉ: "ሰውዬው የአላህ ስም ሳይወሳበት ምግቡን የጀመረ ጊዜ ሸይጧን ምግቡን ለመመገብ ይመቻቻል። እርሱም ይህቺን ሴትዮ ምግቡን ለራሱ ለማስመቸት ይዟት መጣ። እጇንም ያዝኳት። ይህንንም ሰውዬ ምግቡን ለራሱ ለማስመቸት ይዞት መጣ። እጁንም ያዝኩት። ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ! የሸይጧንን እጅ ከሴትዮዋ እጅ ጋር በእጄ ነው።" ካሉ በኋላ የአላህን ስም ካወሱ በኋላ ተመገቡ።