ዑመር ቢን አቢ ሰለማህ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባለቤት የሆነችው የኡሙ ሰለማህ ልጅ ነው። ያደገውም በሳቸው እነፃና እንክብካቤ ስር ነበር። በሚበላበት ወቅት ምግብ ለማንሳት እጁን በእቃው ዙሪያ ያዘዋውር ነበር። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶስት የአመጋገብ ስርአቶችን አስተማሩት: የመጀመሪያው: መብላት ሲጀምር "ቢስሚላሂ" ማለት ነው። ሁለተኛው: በቀኝ መብላት ነው። ሶስተኛው: ለርሱ ቅርብ በሆነ ምግብ በኩል መመገብ ነው።