የተወሰኑ ሶሓቦች ነቢዩን - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ በማለት ጠየቁ: "እኛ እንበላለን። ነገር ግን አንጠግብም።" ነቢዩም - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለነርሱ እንዲህ አሏቸው: "ምን አልባት ስትበሉ ተበታትናችሁ ለየብቻ ነው እንዴ የምትበሉት?" እነርሱም: "አዎን" አሉ። እርሳቸውም: "ተሰብሰቡ ሳትበታተኑ ብሉ። ስትበሉ ቢስሚላህ በማለት የአላህን ስም አውሱ። በዛም ይባረክላችኋልም ትጠግባላችሁም።" አሏቸው።