ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ኢበረኑ ሉትቢያህ የሚባልን ሰውዬ በኒ ሱለይም ከሚባል ጎሳ ዘካ እንዲሰበስብ ሾሙት። ወደ መዲና የተመለሰ ጊዜም ስለሰበሰበውና ስላወጣው ወጪ ተሳሰቡት። ኢብኑል ሉትቢያም እንዲህ አለ: ይህ የሰበሰብኩት የዘካ ገንዘባችሁ ነው። ይህ ደግሞ የተሰጠኝ ስጦታ ነው። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለርሱ እንዲህ አሉት: እውነትህን ከሆነ ስጦታ እንደሚሰጥህ ለማየት እናት አባትህ ቤት አትቀመጥም ነበር? ላንተ ስጦታ እንዲሰጥህ ሰበብ የሆነክ የሰራህበት ስራ ይዞት የመጣው ሹመት ነው። ቤትህ ብትቀመጥ ኖሮ ለአንተ አንዳችም ስጦታ አይሰጥህም ነበር። ስጦታ በሚል ስም አንተ ጋር ስለደረሰ ብቻ ሐላል ልታደርገው አይገባም። ቀጥለውም ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ተቆጥተው ኹጥባ ለማድረግ ወደ ሚንበር ወጡ። አላህን ካመሰገኑና ካወደሱም በኋላ እንዲህ አሉ: ከዚህ በመቀጠል: አላህ ለኔ እንድቆጣጠረው ባደረገኝ ዘካና ምርኮ ላይ ከናንተ መካከል አንድን ሰውዬ ሰራተኛ አደርገዋለሁ። ስራውን አጠናቆ ሲመጣ እንዲህ ይለኛልን!? ይህ ለናንተ ነው ይህ ደግሞ የተሰጠኝ ስጦታ ነው! ስጦታው ቤቱ እንድትመጣለት አባት እናቱ ቤት አይቀመጥም ነበርን!? በአላህ እምላለሁ! ከናንተ መካከል ማናችሁም የወሰደው የምትጮህ ግመል ወይም የምታጋሳ ከብት ወይም የምትጮህ በግ ብትሆን እንኳ የትንሳኤ ቀን ጫንቃው ላይ ተሸክሟት አላህን ቢገናኝ እንጂ ከሚሰጠው ሃላፊነት ያለአግባብ አንዳችን ወስዶ የሚቀር የለም። ዙሪያቸው የተቀመጡ ሰዎች የብብታቸውን ንጣት እስኪመለከቱ ድረስ እጃቸውን በጣም ከፍ አደረጉ። ቀጥለውም እንዲህ አሉ: "አላህ ሆይ! አድርሻለሁ፤ የአላህን ፍርድ ወደናንተ አድርሻለሁ።" ቀጥሎ አቡ ሑመይድ አስሳዒዲይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ይህንን አይኑም ያየችው ጆሮውም የሰማው እንደሆነ ተናገረ።