ሂንድ ቢንት ዑትባ ረዲየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ስለባሏ አቡ ሱፍያን ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና - ነቢዩን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ጠየቀች። እርሱ በገንዘቡ ስስታምና ንፉግ ነበር። እርሱ ሳያውቅ በድብቅ ከገንዘቡ ካልወሰደች በቀር ለርሷና ለልጆቿ የሚበቃትን ወጪ አይሰጣትም ነበር። ይህን በማድረጓ ወንጀል ይኖርባት እንደሁ ጠየቀች። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "ባያውቅ እንኳ በተለምዶ በቂ ነው ተብሎ የተለመደውን ያህል ላንቺና ለልጆቹ ከገንዘቡ ውሰጂ።" አሏት።