ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አንዳንድ የምፅዋት አይነቶችን እንዲህ በማለት አወሱ። "በአላህ መንገድ ለሚደረግ ትግል ወጪ ያደረግከው አንድ ዲናር፣ ከባርነት ነፃ ለማውጣት ወጪ ያደረግከው አንድ ዲናር፣ የሚያስፈልገው ለሆነ ሚስኪን ወጪ ያደረግከው አንድ ዲናር፣ ለቤተሰብህና ለዘመዶችህ ወጪ ያደረግከው አንድ ዲናር ይኖራል።" ቀጥለውም ከነዚህ መካከል አላህ ዘንድ ትልቅ ምንዳ የሚያስገኘው ዲናር ቀለብ ግዴታ ለሆነብህ የቤተሰብ አካል የምታወጣው ወጪ እንደሆነ ተናገሩ።