ከዐብደላህ ቢን ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሚንበር ላይ ሳሉ ስለ ምፅዋት፣ ጥብቅነትና ልመና ካወሱ በኋላ እንዲህ አሉ: "ከላይ ያለች እጅ ከታች ካለች እጅ የተሻለች ናት። ከላይ ያለች እጅ ሰጪዋ ስትሆን ከታች ደግሞ ጠያቂዋ እጅ ናት።"» ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሚንበር ላይ ኹጥባ እያደረጉ ሳሉ ስለ ምፅዋት፣ ጥብቅነትና ልመና ካወሱ በኋላ እንዲህ አሉ: "የምትሰጥ የሆነች ከላይ ያለች እጅ የምትለምን ከሆነች ከታች ካለች እጅ አላህ ዘንድ የተሻለችና ተወዳጅ ናት።"

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ከዚህ ሐዲሥ ለመልካም መንገዶች የመስጠትና የመመፅወትን ትሩፋትና የመለመንን አስከፊነት እንረዳለን።
  • በዚህ ሐዲሥ ከልመና መጠበቅ፣ ከሰዎች መብቃቃት፣ ከፍ ያሉ ነገሮችን እንድንላበስና የወረደን ነገር እንድንተው ተበረታቷል። አላህ ከፍ ያሉ ነገሮችን ይወዳል።
  • እጆች አራት አይነት ናቸው። በደረጃም የሚበላለጡት እንደሚከተለው ነው: ከፍተኛዋ ሰጪ ናት። ቀጥሎ ከመቀበል የተብቃቃች እጅ ናት። ቀጥሎ ሳትለምን የምትቀበል እጅ ናት። ቀጥሎ የመጨረሻዋ የምትለምን እጅ ናት።