ከአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዺየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "የዐብዱረሕማን ቢን ዐውፍ ባለቤት የነበረችው ኡሙ ሐቢባ ቢንት ጀሕሽ የአላህ መልክተኛን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለምታየው ደም ስሞታ አቀረበች። እርሳቸውም 'የወር አበባሽ የሚያግድሽ ቀናት ያክል (ሳትሰግጂ ሳትፆሚ) ቆዪ ከዚያም ታጠቢ።' አሏት። እርሷም ለሁሉም ሶላት ትታጠብ ነበር።" ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።