ሙዓዘተል ዓደዊያህ የአማኞች እናት የሆነችውን ዓኢሻን አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና እንዲህ በማለት ጠየቀቻት: "የወር አበባ ላይ ያለች ሴት ፆምን ቀዷ እያወጣች ሶላትን ቀዷ የማታወጣው ለምንድን ነው?" እርሷም "አንቺ ለማጥበቅና ለማክበድ ጥያቄን የሚያበዙት ከሆኑት ከኸዋሪጆች ከሐሩሪያዎች ነሽን?" አለቻት። እኔም "ሐሩሪያ አይደለሁም። እንዲሁ እየጠየቅኩ ነው።" አልኳት። እርሷም "ከነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ሳለን የወር አበባ ያጋጥመን ነበር። ፆምን ቀዷ በማውጣት ስንታዘዝ ሶላትን ቀዷ በማውጣት ግን አንታዘዝም ነበር።" አለች።