ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የመጨረሻዎቹ አስሩ የረመዷን ቀናት የመጡ ጊዜ በአምልኮና ትርፍ ስራዎች ላይ ጥረት ያደርጉ ነበር። በሌላ ወቅት ይጥሩ ከነበሩት የበለጠ በመልካም ስራ አይነቶች፣ በአምልኮና፣ በበጎ አድራጎት ዘርፎች አበዝተው ይጥሩ ነበር። ይህም እንዚህ ሌሊቶች ያላቸው ደረጃ የላቀና ከፍያለ ስለሆነ እንዲሁም ለይለተል ቀደርንም ለመፈለግ ነው።