ከአማኞች እናት ከዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የረመዿን የመጨረሻዎቹ አስሩ ቀናት የገቡ ጊዜ ሌሊቱን ህያው ሆነው ያሳልፋሉ፤ ቤተሰባቸውንም ያነቃሉ፤ ይበረቱና ሽርጣቸውንም ያጠብቁ ነበር።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።