explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በረመዳን ከመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ የምትገኘው መወሰኛይቱ ሌሊትን (ለይለቱል ቀድርን) የመቆም ትሩፋትን ተናገሩ። በዚህች ሌሊት በሷና ስለሷ ትሩፋት በመጡ ሐዲሦች አምኖ እንዲሁም በስራው ይዩልኝና ይስሙልኝን ሳይሆን የአላህን ምንዳ ከጅሎ በሶላት፣ በዱዓእ፣ ቁርአን በመቅራትና በዚክር የታገለ ሰው ያለፈውን ኃጢዓቱ ይማራል።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • የመወሰኛይቱ ሌሊት (የለይለቱል ቀድር) ትሩፋትና ይህቺን ሌሊት መቆም የሚበረታታ መሆኑን እንረዳለን።
  • መልካም ስራዎች ከእውነተኛ ኒያ ጋር ካልሆነ በቀር ተቀባይነት አያገኙም።
  • የመወሰኛይቱ ሌሊትን (የለይለቱል ቀድርን) አምኖና ምንዳውን አስቦ የቆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ ለሱ መማሩ የአላህን እዝነትና ትሩፋት እንረዳበታለን።