ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መዲና መጥተው ሰዎች የተመለከቷቸው ጊዜ ወደርሳቸው አቅጣጫ በፍጥነት ሄዱ። ዐብደላህ ቢን ሰላምም ያኔ አይሁድ ነበርና ወደርሳቸው ከመጡት መካከል አንዱ ነው። እርሳቸውን ሲያይም በርሳቸው ላይ ብርሃንን፣ ውበትንና እውነተኛ ግርማን በማየቱ ፊታቸው የውሸታም ፊት እንዳልሆነ አወቀ። ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንደበት ለመጀመሪያ የሰማውም ነገር ሰዎችን ጀነት ለመግባት ሰበብ የሚሆናቸውን ተግባራት ላይ ማነሳሳታቸውን ነው። መጀመሪያ: ባወቅከውም ይሁን ባላወቅከውም ሰው ላይ ሰላምታን ማሰራጨትና ማብዛት ነው። ሁለተኛ: ምግብን በሶደቃ፣ በስጦታና በእንግድነት መልክ ማብላት ነው። ሶስተኛ: በአባት ወይም በእናት በኩል ቅርበትና ዝምድና ከምትተሳሰርው አካል ጋር ዝምድናን መቀጠል ነው። አራተኛ: ሰዎች በተኙበት ለሱና (ግዴታ ላልሆነ) ሶላት ሌሊት መቆም ነው።