ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ባልደረቦች የተወሰኑት ለይለቱል ቀድር በረመዷን የመጨረሻዎቹ ሰባት ሌሊቶች ሆና በህልማቸው ተመለከቱ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "ለይለቱል ቀድርን በህልማችሁ በመጨረሻዎቹ የረመዳን ሰባት ቀናት ሆና ማየታችሁ ህልማችሁ ከእውነታው ጋር ገጥማለች ብዬ አምናለሁ። እርሷን ያሰበና ለመፈለግ የጓጓ ሰው በነዚህ ምሽቶች እርሷን ፍለጋ መልካም ስራዎችን በማብዛት ይታገል። እርሷ በመጨረሻዎቹ ሰባት ሌሊቶች እንደምትሆን ተስፋ ይደረጋልና።" ያ ማለት የረመዷን ቀናቶች ሰላሳ የሆኑ ጊዜ ከሀያ አራተኛው ምሽት ይጀምራል። የረመዷን ቀናቶች ሀያ ዘጠኝ የሆኑ ጊዜ ደግሞ ከሀያ ሶስተኛው ሌሊት ይጀምራሉ።